South Ethiopia Regional State Bureau of Planning and Development
ዜና

የክልሉ የኢኮኖሚ ዕድገት ሁኔታ

Nov 19, 2026

በአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ መሠረት የማክሮ ኢኮኖሚ ዋነኛ ዓላማ የግብርና ምርትና ምርታማነት
በማሳደግ አስተማማኝ የምግብ ምርትና የኢንደስትሪ ግብይት አቅርቦት እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ ግኝትን
በማጠናከር ለልማት የተመቻቸ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ በመፍጠር ፈጣን ዘላቂና ፍትሐዊ ዕድገት
ማስመዝገብ ነው፡፡
የክልላችን አጠቃላይ ኢኮኖሚ ሁኔታ አፈፃፀምን በተመለከተ ባለፉት ሶሰት ዓመታት ውስጥ (2013-2015
ዓ.ም) የክልሉ ጠቅላላ ምርት በወቅቱ በነበረ ዋጋ (በ2013 ዓ.ም ዋጋ) ከነበረበት 449.4 ቢሊዮን ብር በ2015
በጀት ዓመት 615.5 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡
እንዲሁም በ2013 ዓ.ም በተመሠረተ ቋሚ ዋጋ የክልሉ ጠቅላላ ምርት በ2013 ዓ.ም ከነበረበት 173.6
ቢሊዮን ብር በ2015 በጀት ዓመት 201.6 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡
በ2013 ዓ, ም በተመሠረተ ዋጋ የክልላችን አጠቃላይ ኢኮኖሚ በ2014 በጀት አመት አጠቃላይ የ6.1 በመቶ"
በ2015 በጀት ዓመት የ6.5 በመቶ ዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ተመዝግቧል፡፡ በዚህም መሠረት የክልላችን
ያለፉት ሶስት ዓመታት አማካይ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገት 6.2 በመቶ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡
የክልሉን የኢኮኖሚ ዕድገት በክፍላተ ኢኮኖሚ ስንመለከት ባለፉት ሶሰት ዓመታት ውስጥ በአማካይ የግብርና
ዘርፍ 6.5 በመቶ፤በኢንዱስትሪ 6.6 በመቶ እና በአገልግሎት ዘርፍ 6 በመቶ እድገት አስመዝግበዋል፡፡
የክልሉን ጠቅላላ ምርት ከክፍላተ ኢኮኖሚ ድርሻ አንፃር ስንመለከት የግብርናው ዘርፍ በ2013 ዓ.ም ከነበረው
45 በመቶ ድርሻ በ2015 ዓ.ም ወደ 45.5 በመቶ ድርሻ በመጠነኛ ሁኔታ ከፍ ያለ ሲሆን የኢንደስትሪው ዘርፍ
በ2013 ከነበረበት 14 በመቶ ድርሻ በ2015 ዓ.ም ወደ 13.5 በመቶ ዝቅ ብሏል፡፡ ይህም ሁኔታ የክልሉ
ኢኮኖሚ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ የሚደረገውን የመዋቅራዊ ሽግግር ሂደት በአግባቡ እያመራ አለመሆኑና
መዋቅራዊ ሽግግሩ ችግር ያለበት መሆኑን ያመለክታል፡፡