South Ethiopia Regional State Bureau of Planning and Development
Photo of Almaz Balta Aboye (PhD)

Almaz Balta Aboye (PhD)

Head Bureau of Plan & Dev't

ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ ይፋዊ ድረ-ገጽ እንኳን በደህና መጡ!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የክልሉን እምቅ የመልማት አቅም በአግባቡ በመለየት፣ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ እና እየተካሄደ ያለውን ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴ በተገቢው አቅጣጫና ፍጥነት በመምራት ህዝባችን የዘላቂ ልማት፣ የዲሞክራሲ እና የመልካም አስተዳደር ትሩፋቶች ተጠቃሚ እንዲሆን በልዩ ትኩረት እየሰራ ይገኛል።

ቢሮአችን በአዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መነሻነት፡-

• ስትራቴጂካዊ እቅድና ቅንጅት፡ የመንግስትን ፖሊሲና ስትራቴጂ የተከተሉ የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ እቅዶችን ያዘጋጃል፤ እንዲሁም የክልሉን መንግስታዊ ተቋማት በማስተባበር ድጋፍና ክትትል ያደርጋል።
• የልማት አቅምና ስነ-ህዝብ፡ የክልሉን እምቅ የልማት አቅም አጥንቶ አሟጦ ለመጠቀም የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችን ይቀይሳል፤ ከኢኮኖሚ እድገት ጋር የተመጣጠነ የሕዝብ ቁጥር እድገት እንዲኖርም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል።
• ፍትሃዊ ተጠቃሚነት፡ የመሰረተ-ልማት ፕሮጀክቶችና የልማት ፕሮግራሞች ስርጭትን ሚዛናዊ በማድረግ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲሰፍንና የሕዝቡ እርካታ እንዲጎለብት በትጋት ይሰራል።
በተጨማሪም ቢሮው የክልሉን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ዲሞግራፊያዊና ጂኦስፓሻል መረጃዎችን በጥራትና በተአማኒነት በማሰባሰብ፣ በማደራጀትና በመተንተን ለፖሊሲ ቀራጮች፣ ለዕቅድ አውጪዎች፣ ለተመራማሪዎችና ለውሳኔ ሰጪዎች ተደራሽ ያደርጋል።

በድረ-ገጻችን አማካኝነት ወቅታዊ የልማት እቅዶችን፣ ስታትስቲካዊና ጂኦስፓሻል መረጃዎችን እንዲሁም የቢሮአችንን ልዩ ልዩ አገልግሎቶች በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። ስለጎበኙን እናመሰግናለን!